Follow US On Social Media
የጌታቸው ረዳ ቃለ መጠይቅ ባጭሩ
የጌታቸው ረዳ ቃለ መጠይቅ ባጭሩ
- የትግራይ ሰራዊት ብቃት መግለፅ ኣይጠበቅብኝም፣ ለህልውናው የሚታገል ብቃት ያለው ሰራዊት ነው።
- እቶቼ ወንድሞቼ፣ ኣባቶቼ እናቶቼ ክብሬ ኣሳልፌ ኣልሰጥም ያለ ሰራዊት ነው።
- በትግራይ ላይ የተቀሰሩ ጣቶች እንዲቆጠቡ የተሰማራ ሰራዊት ነው። ስለ ሰራዊቱ ሚልየን ብንናገር የሚበቃ ኣይመስለኝም።
- በጦርነት ሊዘጉት ያልቻሉትን ጉሮሮ በመብራት፣ በስልክ በመንገድ መዝጋት ሊተገብሩት እየጣሩ ነው።
- ኣማራ ክልል የገባነው እነ ኣገኘሁ እና ኣብይ እንደሚያወሩት ሳይሆን፣ በትግራይ እናቶች የተቀሰሩ ጣቶች ለማስታገስ ነው።
- በገባንባቸው የኣማራ ክልል ከተሞች ህዝቡ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር እያደረግን ነው።
- በገባንባቸው ከተሞች ህዝቡ በደስታ እየተቀበለን ነው፣ በደስታ የሚቀበለን እንደግል ኣዳኝ ቆጥሮን ኣይደለም እህቶቹ እናቶቹ ላይ ሲተኩስ ስላላየው ነው።
- እነ ኣብይ እና ኣገኘሁ ኣንዳንዴ እንደ ኣሸማጋይ፣ ኣንዳንዴ ነብያት ሁነው ለመኖር ነው የሚፈልጉት ግን ኣንፈቅድላቸውም።
- ላሊበላ ስንገባ ላሊበላን እንዳትነኩ ብለው የጠየቁ ኣሉ፣ ስለ ኣክሱም እና ስለ ኣልነጃሺ የተናገረ ግን ማንም ኣልነበረም።
- የትግራይ ሰራዊት ስም ለማጉደፍ እና ታሪካቸውንም ጭምር ምንም ስለ ማይመስላቸው ራሳቸውም ሊመቱት ይችላሉ።
- ህዝቡ የምትፈልጉዋቸው ወንበዴዎች ካሉ ንገሩን ራሳችን መንጥረን እንሰጣቹሃለን እያለን ነው።
- በገባንበት ሁሉ ጠብመንጃው ጭራሮ ኣስመስሎ እየተወያየ ነው።
- ራያና ወልቃይት ከተያዘ ራሴን ኣጠፋለሁ ያለው ኣገኘሁ ተሻገር ኣሁን ወደ ስልጣኔን እለቃለሁ የሚል ቀይሮታል።
- ወልድያ ውግያ እየተካሄደ ቆቦ ይልሻል፣ ጨጨሆ ውግያ እየተደረገ ወልድያ ይልሻል። በዚህ ነው ልሸውዱት የሚፈልጉት።
- እነዚህ ቅርሻቶች ለዚህ ህዝብ እያስተዳድሩ ስታይ ፣ እነዚህ እንዲፈጠሩ ኣስተዋፅኦ ማድረግህ ይቆጭሃል።
- ብልፅግና በራያ ግንባር እያለ ይፎክራል፣ ራያ ግንባር ወፍ የለም።
- ለምንድነው የሚዋሹት? ውሸት የስራቸው ኣልፋና ኦሜጋ ስለሆነ ነው።
- የኣማራ ወጣት የማይክል ጃክሰን they don’t really care about us የሚለውን ዘፈን ሰምተው ለነ ደመቀ ይህንን ነው ማለት ያለባቸው።
- ኣወል ኣርባ የኣብይ የሳሎን ውሻ ነው፣ የኣብይ ፈገግታ ካየ በቃ በዛው ይረካል።
- ዓፋር ክልል ላይ ያለው ጋሊኮማ ኣይደል 10 ሺ ተፈናቃይ፣ እዛ ኣከባቢ 10 የሚያህል ኗሪ የለም።
- ዓፋር ውስጥ ያሉ ወጣቶች ኣታግሉን ነው እያሉን ያሉት።
- ህፃን ኣይገደልብኝ ብሎ የተነሳ ሰራዊት ህፃን በመግደል ትግሉን ኣያሳካም።
- ኣብይ መንግስቱ ሃይለማርያም ለመምሰል የነበረው ፍላጎት በተሟላ መልኩ እየተገለፀበት ያለ ሁኔታ ነው ያለው። መልካቸው ሳይመሳሰል ኣይቀርም ኣሁን።
- ምዕራብ ትግራይ ነፃ እናወጣዋለን። እነሱ ስለ ማይችሉት ለሻዕቢያ ሊሰጡት እየተደራደሩ ናቸው። ሻዕቢያ ይግባ እናሳየዋለን።
- የኣማራ ልዩ ሃይል እየተዋጋ መከላከያ ወደ ኃላ እየሸሸ ብለው ነው የሚያወሩት ፣ ሁሉም እየተዋጉ እየቀጣናቸው ነው ያሸነፍነው።
- የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የቀረው ታንኩ፣የቀረው ሮኬቱ፣የቀረው መድፉ፣ የቀረው ኣሻንጉሊቱ ይዞ ተዋግቷል። ተሟርካል።
- ኣዳዲስ የጦር መሳርያ እየገዛ እንደሆነ መረጃው ኣለን፣ ድሮንም፣ታንክም፣ ዲሽቃም መድፍም እየገዛ ነው፣ እናውቃለን።
- ክተት የተባለው የዘር ማጥፋት ድርጊቱ ህዝባዊ ተሳትፎ እንዲኖረው ተፈልጎ የተሰራ ነው።
- የትግላችን ኣልፋና ኦሜጋ የትግራይ ህዝብ መብት ማስከበር ነው።
- የሰሜን እና የደቡብ ዕዝ ኣዛዦች ክንዱ በዙ፣ ሰለሞን ኢተፋ ላሊበላ ላይ፣ ወልድያ ላይ ምን ሲሰሩ ነበር ብለው ይጠይቋቸው፣ ካገኙዋቸው።
- ተኩስ ኣቁም ላይ ነበርኩ የሚለው ኣብይ፣ ሰራዊቱ ደብረ ዘቢጥ፣ ጨው በር፣ ዓዲ ኣርቃይ፣ ወልድያ ከነ ታንኩ ምን ሲሰራ ነበር?
- እኔ ከሞትኩ ሰርዶ ኣይብቀል የሚለው ለኣህያ ተሰጣት እንጂ፣ ይህንን ድርጊት ለኣብይ ነው የሚገልፀው።
- መወልወያ እና ‘መሽረፈት’ የሚሸጡ የትግራይ ተወላጆች ተግፈተዋል።
- እየሸሸህ መማረክ ኣትችልመ፣ እየተገረፍክ እንዴት ነው የምትማርከው? ሳትዋጋ እንዴት ነው የምትማርከው።
- ብዙዎች እየተጠነቀቃችሁ ከኣብይ መቃብር ብትርቁ መልካም ነው።
ቴሌቪዥን ትግራይ 05 ሓምሌ 05/2013 ኣቆፃፅራ ግዕዝ
Subscribe to:
Posts (Atom)
Report: 150 starved to death in Ethiopia's Tigray in August
Report: 150 starved to death in Ethiopia's Tigray in August A young Tigrayan girl sits on sacks of wheat after the World Food Programme ...
