Follow US On Social Media

የጌታቸው ረዳ ቃለ መጠይቅ ባጭሩ


የጌታቸው ረዳ ቃለ መጠይቅ ባጭሩ

  • የትግራይ ሰራዊት ብቃት መግለፅ ኣይጠበቅብኝም፣ ለህልውናው የሚታገል ብቃት ያለው ሰራዊት ነው።
  • እቶቼ ወንድሞቼ፣ ኣባቶቼ እናቶቼ ክብሬ ኣሳልፌ ኣልሰጥም ያለ ሰራዊት ነው።
  • በትግራይ ላይ የተቀሰሩ ጣቶች እንዲቆጠቡ የተሰማራ ሰራዊት ነው። ስለ ሰራዊቱ ሚልየን ብንናገር የሚበቃ ኣይመስለኝም።
  • በጦርነት ሊዘጉት ያልቻሉትን ጉሮሮ በመብራት፣ በስልክ በመንገድ መዝጋት ሊተገብሩት እየጣሩ ነው።
  • ኣማራ ክልል የገባነው እነ ኣገኘሁ እና ኣብይ እንደሚያወሩት ሳይሆን፣ በትግራይ እናቶች የተቀሰሩ ጣቶች ለማስታገስ ነው።
  • በገባንባቸው የኣማራ ክልል ከተሞች ህዝቡ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር እያደረግን ነው።
  • በገባንባቸው ከተሞች ህዝቡ በደስታ እየተቀበለን ነው፣ በደስታ የሚቀበለን እንደግል ኣዳኝ ቆጥሮን ኣይደለም እህቶቹ እናቶቹ ላይ ሲተኩስ ስላላየው ነው።
  • እነ ኣብይ እና ኣገኘሁ ኣንዳንዴ እንደ ኣሸማጋይ፣ ኣንዳንዴ ነብያት ሁነው ለመኖር ነው የሚፈልጉት ግን ኣንፈቅድላቸውም።
  • ላሊበላ ስንገባ ላሊበላን እንዳትነኩ ብለው የጠየቁ ኣሉ፣ ስለ ኣክሱም እና ስለ ኣልነጃሺ የተናገረ ግን ማንም ኣልነበረም።
  • የትግራይ ሰራዊት ስም ለማጉደፍ እና ታሪካቸውንም ጭምር ምንም ስለ ማይመስላቸው ራሳቸውም ሊመቱት ይችላሉ።
  • ህዝቡ የምትፈልጉዋቸው ወንበዴዎች ካሉ ንገሩን ራሳችን መንጥረን እንሰጣቹሃለን እያለን ነው።
  • በገባንበት ሁሉ ጠብመንጃው ጭራሮ ኣስመስሎ እየተወያየ ነው።
  • ራያና ወልቃይት ከተያዘ ራሴን ኣጠፋለሁ ያለው ኣገኘሁ ተሻገር ኣሁን ወደ ስልጣኔን እለቃለሁ የሚል ቀይሮታል።
  • ወልድያ ውግያ እየተካሄደ ቆቦ ይልሻል፣ ጨጨሆ ውግያ እየተደረገ ወልድያ ይልሻል። በዚህ ነው ልሸውዱት የሚፈልጉት።
  • እነዚህ ቅርሻቶች ለዚህ ህዝብ እያስተዳድሩ ስታይ ፣ እነዚህ እንዲፈጠሩ ኣስተዋፅኦ ማድረግህ ይቆጭሃል።
  • ብልፅግና በራያ ግንባር እያለ ይፎክራል፣ ራያ ግንባር ወፍ የለም።
  • ለምንድነው የሚዋሹት? ውሸት የስራቸው ኣልፋና ኦሜጋ ስለሆነ ነው።
  • የኣማራ ወጣት የማይክል ጃክሰን they don’t really care about us የሚለውን ዘፈን ሰምተው ለነ ደመቀ ይህንን ነው ማለት ያለባቸው።
  • ኣወል ኣርባ የኣብይ የሳሎን ውሻ ነው፣ የኣብይ ፈገግታ ካየ በቃ በዛው ይረካል።
  • ዓፋር ክልል ላይ ያለው ጋሊኮማ ኣይደል 10 ሺ ተፈናቃይ፣ እዛ ኣከባቢ 10 የሚያህል ኗሪ የለም።
  • ዓፋር ውስጥ ያሉ ወጣቶች ኣታግሉን ነው እያሉን ያሉት።
  • ህፃን ኣይገደልብኝ ብሎ የተነሳ ሰራዊት ህፃን በመግደል ትግሉን ኣያሳካም።
  • ኣብይ መንግስቱ ሃይለማርያም ለመምሰል የነበረው ፍላጎት በተሟላ መልኩ እየተገለፀበት ያለ ሁኔታ ነው ያለው። መልካቸው ሳይመሳሰል ኣይቀርም ኣሁን።
  • ምዕራብ ትግራይ ነፃ እናወጣዋለን። እነሱ ስለ ማይችሉት ለሻዕቢያ ሊሰጡት እየተደራደሩ ናቸው። ሻዕቢያ ይግባ እናሳየዋለን።
  • የኣማራ ልዩ ሃይል እየተዋጋ መከላከያ ወደ ኃላ እየሸሸ ብለው ነው የሚያወሩት ፣ ሁሉም እየተዋጉ እየቀጣናቸው ነው ያሸነፍነው።
  • የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የቀረው ታንኩ፣የቀረው ሮኬቱ፣የቀረው መድፉ፣ የቀረው ኣሻንጉሊቱ ይዞ ተዋግቷል። ተሟርካል።
  • ኣዳዲስ የጦር መሳርያ እየገዛ እንደሆነ መረጃው ኣለን፣ ድሮንም፣ታንክም፣ ዲሽቃም መድፍም እየገዛ ነው፣ እናውቃለን።
  • ክተት የተባለው የዘር ማጥፋት ድርጊቱ ህዝባዊ ተሳትፎ እንዲኖረው ተፈልጎ የተሰራ ነው።
  • የትግላችን ኣልፋና ኦሜጋ የትግራይ ህዝብ መብት ማስከበር ነው።
  • የሰሜን እና የደቡብ ዕዝ ኣዛዦች ክንዱ በዙ፣ ሰለሞን ኢተፋ ላሊበላ ላይ፣ ወልድያ ላይ ምን ሲሰሩ ነበር ብለው ይጠይቋቸው፣ ካገኙዋቸው።
  • ተኩስ ኣቁም ላይ ነበርኩ የሚለው ኣብይ፣ ሰራዊቱ ደብረ ዘቢጥ፣ ጨው በር፣ ዓዲ ኣርቃይ፣ ወልድያ ከነ ታንኩ ምን ሲሰራ ነበር?
  • እኔ ከሞትኩ ሰርዶ ኣይብቀል የሚለው ለኣህያ ተሰጣት እንጂ፣ ይህንን ድርጊት ለኣብይ ነው የሚገልፀው።
  • መወልወያ እና ‘መሽረፈት’ የሚሸጡ የትግራይ ተወላጆች ተግፈተዋል።
  • እየሸሸህ መማረክ ኣትችልመ፣ እየተገረፍክ እንዴት ነው የምትማርከው? ሳትዋጋ እንዴት ነው የምትማርከው።
  • ብዙዎች እየተጠነቀቃችሁ ከኣብይ መቃብር ብትርቁ መልካም ነው።

ቴሌቪዥን ትግራይ 05 ሓምሌ 05/2013 ኣቆፃፅራ ግዕዝ

No comments:

Post a Comment

Report: 150 starved to death in Ethiopia's Tigray in August

Report: 150 starved to death in Ethiopia's Tigray in August A young Tigrayan girl sits on sacks of wheat after the World Food Programme ...